Gambella Media Network

Gambella Media Network Total Reliable News Sources, Information and Entertainment Centre

Gambella Media Network (GMN) is an independent non-profit private global media outlet online news, information, interview , entertainment and video portal focusing on current events making network dedicated to promoting the unity and peace with in a world community and freedom of expression in general.

87 years old, Colonel Mengistu Haile Mariam who lives in 🇿🇼Harare, Zimbabwe is an 🇪🇹Ethiopian former politician and form...
01/17/2025

87 years old, Colonel Mengistu Haile Mariam who lives in 🇿🇼Harare, Zimbabwe is an 🇪🇹Ethiopian former politician and former Derg officer who was the president of the People's Democratic Republic of Ethiopia (PDRE) from 1987 to 1991.

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት (🇪🇹Ethiopian National Parliament) በሕዝብና በመንግሥት መካከል መቀራረብ፣ መነጋገር፣ መግባባት እንጂ በግንብ የተከለለ የፖለቲካ ሕይወት አ...
01/13/2025

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት (🇪🇹Ethiopian National Parliament) በሕዝብና በመንግሥት መካከል መቀራረብ፣ መነጋገር፣ መግባባት እንጂ በግንብ የተከለለ የፖለቲካ ሕይወት አያስፈልግም፤ የቤተ መንግሥቱ ለሕዝብ ክፍት መሆንም የዚህ አዲስ የፖለቲካ ዕሳቤያችን ሁነኛ ትእምርት ነው፡፡

አዲስ አበባ፤ ጥር 3/2017 ፦ 🇪🇹ኢትዮጵያ እና 🇸🇴ሶማሊያ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ከስምምነት ላይ ደረሱ።ሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማሻሻል...
01/11/2025

አዲስ አበባ፤ ጥር 3/2017 ፦ 🇪🇹ኢትዮጵያ እና 🇸🇴ሶማሊያ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ከስምምነት ላይ ደረሱ።

ሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማሻሻል በቁርጠኝነት እንደሚሰሩም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ መንግስት የጋራ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድን በደማቅ ሁኔታ አቀባበል አድርገዋል።

የሁለቱ አገራት መሪዎች ዛሬ በአዲስ አበባ የጋራ ፍላጎታቸው በሆኑ የተለያዩ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳቦች መለዋወጣቸውን የጋራ መግለጫው አመልክቷል።

የአገራቱን ህዝቦች የወንድማማችነት ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

በውይይቱ ሁለቱ አገራት በየአገራቱ ያላቸው ሙሉ የዲፕሎማሲ ውክልና በመመለስ ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ነበረበት ለመመለስ እና ለማሻሻል ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

የአገራቱ መሪዎች የዲፕሎማሲ ሚሲዮኖቻቸው በባለብዝሃ ወገን እና በቀጣናዊ ፎረሞች ላይ የሀገራቱ የጋራ ፍላጎቶች ላይ በቅርበት መስራት እንዳለባቸው አጽንኦት የሰጡበት ጉዳይ እንደሆነ ነው በመግለጫው ላይ የተጠቆመው።

መሪዎቹ ለቀጣናው መረጋጋት የሁለቱ አገራት በጋራ መተማመን፣ ተአማኒነት እና መከባበር ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ትብብር እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል።

በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማሻሻል፣ የጋራ መግባባት ለመፍጠርና የጋራ ግቦችን እውን ለማድረግ በትብብር ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በተጨማሪም በውይይቱ ላይ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የጸጥታና ደህንነት ትብብራቸውን ለማጠናከር ቀጣይነት ያለው ስራ ማከናወን እንደሚያስፈልግ ተመላከቷል።

በየጊዜው እየደገ የመጣው እና አሳሳቢ የሆነው የታጠቁ ቡድኖች በቀጣናው ላይ የደቀኑት ስጋት በውይይቱ ላይ ተነስቷል።

የአገራቱ መሪዎች የጸጥታ ተቋማቶቻቸው መመሪያ በመስጠት ቀጣናዊ ሰላም እና መረጋጋት ያላቸውን ትብብር እንዲያጠናክሩ ለማድረግ ተስማማተዋል።

በተጨማሪም መሪዎቹ ሁለቱ አገራት በኢኮኖሚ፣ ኢንቨስትመንት እና ንግድ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ጠንካራ የኢኮኖሚ ትብብር በመፍጠር የንግድ ትስስራቸውን የሚያሳልጡ የመሰረተ ልማት መስመሮችን ለማስፋት እና የጋራ ብልጽግናቸውን ለማረጋገጥ ከስምምነት ላይ መድረሳቸው በጋራ መግለጫው ላይ ተጠቅሷል።

መሪዎቹ ለአንካራው ስምምነት ትግበራ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገልጸው ስምምነቱ ከአገራቱ የወዳጅነት እና የአጋርነት መንፈስ የመነጨ መሆኑን አንስተዋል።

በስምምነቱ የተቀመጠውን የቴክኒክ ድርድሮች በፍጥነት እንዲጀመሩ ለማድረግ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን የጋራ መግለጫው ማመላከቱን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል። Source: ENA

01/11/2025
🇪🇹እንኳን ✝️⛪️🙏ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ, PM Abiy Ahmed  ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን ሕግ ጥሶ ከእግዚአብሔር ጋር የታጣላው ራሱ የሰው ልጅ ነበረ፡፡ ዕርቅን...
01/06/2025

🇪🇹እንኳን ✝️⛪️🙏ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ, PM Abiy Ahmed

ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን ሕግ ጥሶ ከእግዚአብሔር ጋር የታጣላው ራሱ የሰው ልጅ ነበረ፡፡ ዕርቅን አውርዶ ሰላምን ለማስፈን በረት ድረስ የመጣው ግን እግዚአብሔር ነው፡፡ እንደ ቅዱሳት መጻሕፍት አስተምህሮ እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ፣ አሸናፊ፣ የሚሳነው አንዳች የሌለ ነው፡፡ ነገር ግን ለዕርቅ እና ለሰላም ሲል ወደ ማይገባው ሥፍራ መጣ፡፡ አሸናፊ ቢሆንም እንደ ተሸናፊ ሆነ፡፡ ዐቅም ቢኖረው እንደ ዐቅመ ቢስ ሆኖ ታየ፡፡ በሁሉ ሀብታም ሲሆን፣ ራሱን ታናሽ አደረገ፡፡ ይህ ሁሉ ለዕርቅና ለሰላም የተከፈለ የታላቅነት ዋጋ ነው፡፡

እግዚአብሔር ለዕርቅ እና ለሰላም ሲል በደካማዋ ከተማ በቤተልሔም፣ በተናቀችው ሥፍራ በበረት መገኘቱ የገባቸውም ያልገባቸውም ነበሩ፡፡ የገባቸው፤ ከሰማየ ሰማያት ወርደው “ሰላም እና ዕርቅ በምድር ይሁን” ብለው ዘመሩ፡፡ የገባቸው፤ ከምሥራቅ ኮከቡን አይተው፣ እጅ መንሻውን ይዘው መጡ፡፡ የገባቸው፤ በረታቸውን ለቅቀው ለድንግል ማርያም እና ለኢየሱስ ክርስቶስ ሰጡ፡፡ የገባቸው፤ የሰማይ መላእክቱን ተከትለው ወደ በረት ሄደው እርቅና ሰላምን አመሰገኑ፡፡

ያልገባቸው ሰዎች፣ የዕርቅ እና የሰላሙ ዐዋጅ እየታወጀ እነርሱ ግን ተኝተው ነበር፡፡ የመንደር ጌቶች እነ ሄሮድስ፣ የሰው ልጅ ሰላም ማግኘት ሳይሆን ከጠላት ያገኙት ሥልጣን ያስጨንቃቸው ነበር፡፡ የይሁዳ ሰዎች፤ ዓለም በማይመለስበት ሁኔታ እየተቀየረ፣ እነርሱ ግን እየሆነ ያለውን ለውጥ አያዩም አይሰሙም ነበር፡፡ ከሰማይ መላእክት ወርደው፣ ከምድር እረኞች ነቅተው ተአምር ሲሠራ፤ እነርሱ ግን በዕንቅልፍ ደንዝዘው ነበር፡፡እ ነርሱ እያንቀላፉ ከተማቸው ቤተልሔም ተቀይራለች፡፡ የእንጀራ ቤት ሆናለች፡፡ ታሪኳ ተቀይሯል፡፡ ታናሽ ከተማነቷ ተቀይሯል፡፡

ያልገባቸው፣ ሰላምና ዕርቅ ሲባሉ የድካምና የዐቅመ ቢስነት ምልክት አድርገው ተመለከቱት፡፡ ሰይፍና ጎራዴ የለመዱ፤ መግደልና ማጥፋት ጀግንነት የሚመስላቸው ነበሩና፡፡ ሰላም ድካም፣ ዕርቅም ሽንፈት ይመስላቸው ነበር፡፡ ስለዚህም በእኩለ ሌሊት ከመሸ፣ በከብቶች በረት ለሁሉ የመጣውን ሰላም አቅለው አንቀበልም አሉ፡፡ እነ ሄሮድስ ሰይፍ መዘዙ፡፡ ሰላምን አሳደዱ፤ ሰላማዊ ሕጻናትንም ፈጁ፡፡ ሄሮድስ የገዛ ሕዝቡን ለመጨፍጨፍና ለመግዛት በጠላት የተሾመ ሰው ነበር፡፡ የሚያስፈጽመው የእሥራኤል ጠላቶችን ዓላማ ነበረ፡፡

ይሄንን በዓል የምናከብር፤ ወይ ሰላምና ዕርቅን ከሚወዱት ወገን ነን፡፡ አለያም ሰላምንና ዕርቅን ከሚያሳድዱት ወገን ነን፡፡ መንግሥት ሰላምና ዕርቅን ደጋግሞ የሚያውጀው ዐቅም ከማጣት፣ ጉልበቱ ከመድከም የተነሣ አይደለም፡፡ ሁሉም ዓይነት መንግሥታዊ ዐቅሞች በእጁና በደጁ አሉ፡፡ ሰላምና ዕርቅ ግን ከሁሉ በበለጠ፤ ዘመን አሻጋሪ፣ ታሪክ ቀያሪ፣ የችግርና መከራ ዘመን ማብቂያ መፍትሔዎች በመሆናቸው ነው፡፡ ሁሉን አሸናፊ፣ ሁሉን አሻጋሪ ያደርጋሉ፡፡ ጠባሳ ሳይተዉ ቁስልን ያሽራሉ፤ ለልጅ ልጅ ቂምን ሳይሆን ሐሴትን ያወርሳሉ፤ ከመጠፋፋት ይታደጋሉ፡፡ የሰላምና የዕርቅ መንገድ የሚመረጠውም ለዚህ ነው፡፡

ሰላምና ዕርቅን መምረጥ፤ የኃያል ባለ-ራዕይ፣ የፍጹማዊ-አሸናፊና ባለታላቅ-ዐቅም በውዴታ የሚሸከመው የከፍታ ግዳጅ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ ይችል ነበር፡፡ ሰላምን እያወጀ ወደ ከብቶች በረት የመጣው ግን እርሱ ኃያሉ ነው፡፡ የአዳም ልጆች በሠገነት ሲወለዱ የእግዚአብሔር ልጅ ነው በበረት የተወለደው፡፡ እግዚአብሔር ነው ለሰላምና ለዕርቅ ሲባል ከቤተልሔም እስከ ቀራንዮ መከራን የተቀበለው፡፡
መንግሥት ዛሬም ለሰላም እና ለዕርቅ እጁ እንደተዘረጋ ነው፡፡ ለሁሉ የሚሆን ሰላም በኃይል ሳይሆን በፍቅር መንገድ እንደሚመጣ ያውቃል፡፡ ለሰላምና ለዕርቅ በመሸነፍ ውስጥ ፍጹማዊ ማሸነፍ እንዳለ ያምናል፡፡ ጥቂቶች እንጂ ብዙኃኑ ከሰላም የሚገኘውን ክፍያ የሚሹ እንደሆነ ይረዳል፡፡
የጠላት መሣሪያ የነበረውን የሄሮድስን መጨረሻ ማየት ነው፡፡ ለሰላምና ለዕርቅ ጀርባቸውን የሰጡ የቤተልሔም ከተማ ሰዎችን ፍጻሜ ማሰብ ነው፡፡ እግዚአብሔር በረት ድረስ ሲፈልጋቸው አሻፈረኝ ብለው ነበር፡፡ ከዓመታት በኋላ በኃይልና በጉልበት ሲጎበኛቸው ግን፣ ፈልገው ሊያገኙት አልቻሉም፡፡ ቤታቸው የተፈታ ሆኖ ቀረ፡፡ ከዚያ በኋላ ፍለጋቸው መባከንና መቅበዝበዝ ሆነ ፡፡ ዕርቅና ሰላምን የሚገፋ ሁሉ መጨረሻው እንደዚህ ነው፡፡

ሁሉም ጊዜ አለው፡፡ በጊዜው መጠቀም የጠቢባን ድርሻ ነው፡፡ ለሰላም የተዘረጉ እጆች እንደተዘረጉ አይቀሩም፡፡ ለሰላም ሲባል ወደ ምድር የወረዱ ሁሉ እንደ ወረዱ አይቀሩም፡፡ ለሰላም ሲባል ደካሞች መስለው የታዩ ሁሉ፣ ኃይላቸው በጊዜው ይገልጣሉ፡፡ የግድግዳው ጽሑፍ ይመጣል፡፡ የተዘረጋው ብራና ይጠቀለላል፡፡

ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ሦስቱ ሰላማውያን ቦታ አላገኙም ነበር፡፡ የጥበብ ሰዎች፣ እረኞች እና መላእክት፡፡ ሦስቱም ብዙዎቹ ያደረጉትን ለማድረግ የመጡ አልነበሩም፡፡ ትክለኛውን ነገር ለማድረግ እንጂ፡፡ ሦስቱም ዘመን የወለደውን ጊዜ የወደደውን አልተከተሉም፡፡ የሚጠቅመውን ነገር እንጂ፡፡ ታሪክ እንደሚያስተምረን ግን የእነዚህ የሦስቱ እውነት በጊዜው ተገልጧል፡፡ ዓለምም በየዓመቱ የክርስቶስን ልደት ሲያከብር እነዚህን ሦስቱን ሰላማውያን ያስታውሳል፡፡

ለሰላም ስትሉ ዋጋ የምትከፍሉ፣ የምትዋረዱና የምትቃለሉ ሁሉ ከሦስቱ ሰላማውያን መማር አለባችሁ፡፡ የጠላት መሣሪያዎች የሆኑት ሄሮድሳውያን ቢገድሉም፤ የቤተልሔም ሰዎች እምቢ ቢሉም፣ የተማሩ የተባሉት የአይሁድ ሊቃውንት ቢቀልዱም፣ ለሰላም ዋጋ መክፈል ያዋጣል፡፡ ቢያንስ ሰማያዊና ታሪካዊ ዋጋ ያስገኛል፡፡

ይሄንን በዓል ስናከብር ከሦስቱ ሰላማውያን ጋር ሆነን ሰላምና ዕርቅ በሀገራችን እንዲሰፍን የበኩላችንን በማድረግ እንዲሆን ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡ እርስ በርስ ከመሸናነፍ ስለሰላም ሁላችንም ብንሸነፍ ሁላችንንም አሸናፊ ያደርገናል፡፡ መንግሥት ለሰላማዊ መንገዶች ቅድሚያ ይሰጣል፡፡ ለሰላም ከሚሠሩት ጋር ሁሉ አብሮ ይሠራል፡፡ ሰላማውያን ለሚከፍሉት መሥዋዕትነት ክብርና ዋጋ ይሰጣል፡፡


በድጋሜ መልካም በዓል ይሁን፡፡


ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ታህሳስ 28፣ 2017 ዓ.ም

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋምቤላ ገቡ።(ታህሳስ 24/2017 ዓ.ም  ሚኒስትሩ ጋምቤላ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ፣ ምክትል ርዕሰ መ...
01/02/2025

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋምቤላ ገቡ።

(ታህሳስ 24/2017 ዓ.ም ሚኒስትሩ ጋምቤላ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ጋትሉዋክ ሮን፣ የብልፅግና ፓርቲ ጋምቤላ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አሽኔ አስቲን፣ የትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ኡኩኝ ኡኬሎ እንዲሁም የጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ድሪባ ኢቲቻን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች አቀባበል አድርገዉላቸዋል።

ሚኒስትሩ በሚኖራቸው ቆይታ የትምህርት ተቋማትን እንደሚጎበኙ እንዲሁም ከአመራሮች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
Source: ከጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት

Remembering 🇺🇲President Jimmy Carter in 🇪🇹Ethiopia and Middle East. December 29, former President Jimmy Carter  passed a...
12/31/2024

Remembering 🇺🇲President Jimmy Carter in 🇪🇹Ethiopia and Middle East.
December 29, former President Jimmy Carter passed away at the age of 100. As the 39th president of the United States and as a private citizen, Carter was an advocate for peace between nations, democracy and various humanitarian and environmental causes. But in the Middle East, he is going to be remembered as the father of Arab-Israeli normalisation.

Sworn in as president in 1977, Carter was given the opportunity by Egyptian President Anwar Sadat to be the architect of the first normalisation deal between an Arab country and the Jewish state of Israel. He helped Sadat and Israeli Prime Minister Menachem Begin conclude the 1978 Camp David Accords and negotiate the 1979 Egyptian-Israeli peace treaty that formally ended the conflict between the two countries.

At least 71 people died in 🇪🇹Sidama, Ethiopia, when a passenger-loaded truck fell into a river in the Bona district of t...
12/30/2024

At least 71 people died in 🇪🇹Sidama, Ethiopia, when a passenger-loaded truck fell into a river in the Bona district of the Sidama region, according to regional authorities.

Passenger ✈️plane crashes at 🇰🇷South Korean airport, killing 179Most of the 181 people on board are presumably dead, mak...
12/29/2024

Passenger ✈️plane crashes at 🇰🇷South Korean airport, killing 179

Most of the 181 people on board are presumably dead, making it one of the worst aviation disasters to hit South Korea.
At least 176 people have been killed when a passenger plane caught fire after skidding off a runway and slamming into a concrete fence at a South Korean airport.
Two crew members were rescued after the accident that occurred on Sunday at 9:03am local time (00:03 GMT).
The Ministry of Land, Infrastructure and Transport said the plane a 15-year-old Boeing 737-800 jet was returning from Bangkok, and its passengers included two Thai nationals.

The bond between 🇪🇹Ethiopia and 🇫🇷France is built on a shared history of collaboration, a partnership rooted in mutual r...
12/22/2024

The bond between 🇪🇹Ethiopia and 🇫🇷France is built on a shared history of collaboration, a partnership rooted in mutual respect and a commitment to progress. For generations, France has stood alongside Ethiopia, championing our social and economic development with unwavering support.

President Emmanuel Macron’s visit is more than a symbolic gesture it is a reaffirmation of the enduring friendship between our nations. His presence here speaks to the strengthening of our diplomatic ties and the promise of an even brighter future together.

We are deeply grateful to the French government for their pivotal role in preserving Ethiopia's cultural heritage, including the remarkable restoration of the Lalibela churches and the historic Jubilee Palace. These efforts are a testament to France's appreciation for our history and its commitment to our shared legacy.

የጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክን ለማልማት የሚያስችል የአጋርነት ሥምምነት ተፈረመ  ታኅሳስ 2/2017 ፦ የጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ የረጅም ጊዜ ጥበቃና የልማት አስተዳደር ማካሄድ የሚያስችል የሦስትዮሽ...
12/13/2024

የጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክን ለማልማት የሚያስችል የአጋርነት ሥምምነት ተፈረመ

ታኅሳስ 2/2017 ፦ የጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ የረጅም ጊዜ ጥበቃና የልማት አስተዳደር ማካሄድ የሚያስችል የሦስትዮሽ የአጋርነት ሥምምነት ዛሬ በአዲስ አበባ ተፈረመ፡፡

የሦስትዮሽ የአጋርነት ሥምምነቱ የተፈረመው በኢትዮጵያ የዱር እንሥሳት ጥበቃ ባለሥልጣን፣ በጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ አስተዳደር እና በአፍሪካን ፓርኮች መካከል ነው።

ሥምምነቱንም በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ፣ የኢትዮጵያ ዱር እንሥሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኩማራ ዋቅጅራ እና የአፍሪካ ፓርኮች ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፒተር ፈርንሄድ ፈርመውታል።

የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ፣ በአውሮፓ ኅብረት ትብብር የኢትዮጵያ ተወካይ ሮቤርቶ ሽሊሮ እና ሌሎች እንግዶች ደግሞ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት፤ የጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ ሰፊና እምቅ የብዝሃ ህይወት ያለበት ነው።

ይሁን እንጂ ባለው አቅም ልክና በሚፈለገው ደረጃ ባለመልማቱ ከዘርፉ የሚጠበቀውን ጥቅም ማግኘት ሳይቻል ቆይቷል።

አሁን የተደረሰው ስምምነት የክልሉን የዱር እንሥሳት ጥበቃ ዘርፍን ትርጉም ባለው መልኩ ለውጥ የሚያመጣ ነው ብለዋል።

የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ በበኩላቸው መንግሥት ለቱሪዝም ዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት የተፈጥሮ ኃብቶችን በአግባቡ አልምቶ ጥቅም ላይ ለማዋል ጥረት እየተደረገ ነው።

በተለይም የቱሪዝም ኃብቶችን በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በማስተሳሰር የመጠበቅና የማልምት ሥራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ከአፍሪካ ፓርክ ጋር የተፈፀመው ሥምምነት የበለጠ አቅም የሚፈጥር መሆኑንም ተናግረዋል።

የጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክን ከሌሎች የአፍሪካ ፓርኮች ጋር በማስተሳሰር በዘላቂነት ለማልማት የተጀመረው ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።

የመግባቢያ ስምምነቱ የመጪው ትውልድን ጭምር የሚጠቅም እንደሆነ የተናገሩት ደግሞ የአፍሪካ ፓርኮች ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፒተር ፈርንሄድ ናቸው።

ሥምምነቱ የፓርኩን አጠቃላይ ሥነ-ምህዳር ለመጠበቅና ለማልማት ያለመ ሲሆን የአካባቢው ማኅበረሰብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።

በአውሮፓ ኅብረት ትብብር የኢትዮጵያ ተወካይ ሮቤርቶ ሽሊሮ ሥምምነቱ ድንበር ተሻጋሪ የዱር እንሥሳት ስደትን መከላከል የሚያስችል መሰረት የተጣለበት ነው ብለውታል።

በተጨማሪ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በሰውና በተፈጥሮ የሚያጋጥሙ ጉዳቶች ለመከላከል የሥምምነቱ ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዱር እንሥሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኩማራ ዋቅጅራ የጋምቤላ ፓርክ ከደቡብ ሱዳን የሚዋሰንና ብርቅዬ የዱር እንሥሳት ኃብት ያለው መሆኑን ጠቅሰዋል።

ይህ ፓርክ የዓለም ህዝቦች የጋራ ኃብት መሆኑን በመግለጽ የማልማትና የመጠበቅ ሥራ በትብብር መስራት ተገቢነት አለው ብለዋል። Source: Ethiopian News Agency(ENA)

🇪🇹የኢትዮጵያ እና 🇸🇴የሶማሊያ ድርድር በስምምነት ተጠናቀቀ  🇹🇷በቱርኪዬ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን አደራዳሪነት በአንካራ ለሶስተኛ ጊዜ የተካሄደው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ድርድር  ...
12/12/2024

🇪🇹የኢትዮጵያ እና 🇸🇴የሶማሊያ ድርድር በስምምነት ተጠናቀቀ

🇹🇷በቱርኪዬ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን አደራዳሪነት በአንካራ ለሶስተኛ ጊዜ የተካሄደው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ድርድር ሁለቱንም አገራት በሚያግባባ ስምምነት ተጠናቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በቱርኪዬ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋን ግብዣ ዛሬ ምሽት በአንካራ ውይይት አድርገዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች ውይይቱን ካደረጉ በኋላም በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

መሪዎቹ በመግለጫቸው ኢትዮጵያ በሶማሊያ የባሕር ዳርቻ በኩል ዘላቂና ደኅንነቱ የተጠበቀ የወደብ አማራጭ በምታገኝበት አማራጭ ላይ የቴክኒክ ውይይቶችን ለመጀመር መስማማታቸውን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመግለጫቸው፤ ቱርኪዬ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እንዲሰፍን ለምታደርገው ከፍተኛ አስታዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያና የሶማሊያ ህዝቦች በቋንቋ፣ በባህል እና በደም የተሳሰሩ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለጋራ ሰላምና ልማት ከሶማሊያ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗንም ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐመድ በበኩላቸው፤ የሶማሊያ መንግስት የኢትዮጵያ ወታደሮች ለሶማሊያ ሰላም የከፈሉትን መስዋዕትነት አይዘነጋም ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በቀጣይም ሰላምን ለማፅናት በሚያደረጉት ጥረት መንግስታቸው ቁርጠኛ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን በበኩላቸው፤ ሁለቱ ሃገራት የፈረሙት ሰነድ ትብብርን፣ የኢኮኖሚ እድገትን እና ብልጽግናን የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ Source: Ethiopian News Agency (ENA)

🇪🇹🙏❤️19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በአርባምንጭ ከተማ መከበር ጀምሯል። ምክር ቤት ሚያዝያ 21 ቀን 1998 ዓ.ም ባካሔደው ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባው ሕገ-...
12/07/2024

🇪🇹🙏❤️19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በአርባምንጭ ከተማ መከበር ጀምሯል።

ምክር ቤት ሚያዝያ 21 ቀን 1998 ዓ.ም ባካሔደው ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባው ሕገ-መንግሥቱ የጸደቀበት ኅዳር 29 የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ተብሎ በአገር አቀፍ ደረጃ እንዲከበር ወስኗል።

የመጀመሪያው 1ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በ1999 ዓ.ም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አዘጋጅነት በአዲስ አበባ የተከበረ ሲሆን መሪ ሀሳቡም ''ሕገ-መንግሥታዊ ቃል ኪዳን የአብሮነታችን መገለጫ ነው'' የሚል ነበር።

2ኛው የኢትዮጵያ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በኢትዮጵያ ሚሊኒየም በ2000 ዓ.ም በሃዋሳ ''ልዩነታችን ውበታችን ውበታችን አንድነታችንና ጥንካሬያችን ነው'' በሚል መሪ ሀሳብ ተከብሯል።

3ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በ2001 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አዘጋጅነት በአዲስ አበባ የተከበረ ሲሆን መሪ ሀሳቡም ''ዴሞክራሲያዊ አንድነታችንን በማጠናከር ልማታችንን እናፋጥናለን'' የሚል ነበር።

በ2002 ዓ.ም 4ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በድሬዳዋ አስተዳደር አዘጋጅነት ኦሮሚያ፣ አፋር፣ ሶማሌና ሐረሪ ክልሎችና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን ''መቻቻል ለዴሞክራሲያዊ አንድነትና ልማት'' በሚል መሪ ሀሳብ ተከብሯል።

አዲስ አበባ ከተማ በ2003 ዓ.ም 5ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በድጋሜ ለማዘጋጀት ዕድሉን ያገኘች ሲሆን ''የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እጅ ለእጅ ተያይዘን የአገራችንን ህዳሴ ወደማይቀለበስበት ደረጃ እናደርሳለን'' በሚል መሪ ሀሳብ በዓሉ ተከብሯል።

6ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በትግራይ ክልል አዘጋጅነት በመቀሌ በ2004 ዓ.ም ሲከበር መሪ ሀሳቡም ''ሕገ መንግሥታችን ለብዝሃነታችን ለአንድነታችንና ለሕዳሴችን'' የሚል ነበር፡፡

7ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በ2005 ዓ.ም በአማራ ክልል በባህር ዳር ከተማ “ብዙም አንድም ሆነን በመለስ ራዕይ በሕገ-መንግሥታችን ለሕዳሴያችን” በሚል መሪ ቃል መከበሩ የሚታወስ ነው።

8ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ያስተናገደችው የሶማሌ ክልል መዲና ጅግጅጋ ከተማ ስትሆን ''ሕገ-መንግሥታችን ለህዳሴያችን'' በሚል መሪ ሀሳብ በ2006 ዓ.ም ተከብሯል።

9ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ በ2007 ዓ.ም ተከብሯል። መሪ ቃሉም ''በሕገ-መንግሥታችን የደመቀው ኢትዮጵያዊነታችን ለህዳሴያችን'' የሚል ነበር።

10ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በጋምቤላ በ2008 ዓ.ም ሲከበር መሪ ሀሳቡም ''የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ተሳትፎ ለላቀ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን'' የሚል ነበር።

11ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ደግሞ ''ሕገ- መንግሥታችን ለዴሞክራሲያዊ አንድነታችንና ለህዳሴያችን'' በሚል መሪ ሀሳብ በ2009 ዓ.ም በሐረሪ ክልል ተከብሯል።

12ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል "በሕገ-መንግሥታችን የደመቀ ኅብረ-ብሔራዊነታችን ለህዳሴያችን" በሚል መሪ ሃሳብ በ2010 ዓ.ም በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ነበር የተከበረው።

13ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓልን አዲስ አበባ ለሦስተኛ ጊዜ በ2011 ዓ.ም ያስተናገደች ሲሆን የበዓሉ መሪ ቀልም ''በብዝሃነት የደመቀ ኢትዮጵያዊ አንድነት'' የሚል ነበር።

14ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በ2012 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ "ሕገ-መንግሥታዊ ቃልኪዳናችን ለዘላቂ ሰላም" በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።

15ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በ2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አዘጋጅነት "እኩልነትና ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት ለጋራ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ ተከብሯል።

16ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በ2014 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ አስተጋጅነት የተከበረ ሲሆን መሪ ቃሉም “ወንድማማችነት ለኅብረ-ብሔራዊ አንድነት” የሚል ነበር።

17ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል “ሕብረ ብሔራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን” በ2015 ዓ.ም በሚል መሪ ቃል በሲዳማ ክልል ሃዋሳ ከተማ ተከብሯል።

18ኛው የብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን "ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሀሳብ በ2016 ዓ.ም በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ነበር የተከበረው።

19ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን "ሀገራዊ መግባባት ለኅብረ-ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል በአገር አቀፍ ደረጃ አርባ ምንጭ ከተማ ታስተናግዳለች።

12/01/2024
11/30/2024
11/29/2024
11/27/2024
11/25/2024

Address

Calgary
Calgary, AB

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gambella Media Network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Gambella Media Network:

Videos

Share

Our Story

Gambella Media Network (GMN) is an independent non-profit private global media outlet online news, information, interview , entertainment and video portal focusing on current events making network dedicated to promoting the unity and peace with in a world community and freedom of expression in general.